English-amharic Science And Technology Glossary


E-Book Content

እንግሊዝኛ-አማርኛ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሙዳየ-ቃላት - መቅድም ቅዳሜ፣ ሰኔ 8፣ 2005 እ.ኢ.አ፦ “Language shapes the way we think, and determines what we can think about.” - Benjamin Lee Whorf - ቤንጃሚን ሊ ዎርፍ - «ቋንቋ የምናስበውን ፈይዶ ይቀርፃል፣ እናም ልናስብ የምንችለውን ገደብ በይኖ ይወስናል።» - “In a sense, every form of expression is imposed upon one by social factors, one's own language above all.” - Edward Sapir - «በአንድ በኵል፣ ሁሉ የመግባቢያ ዘይቤ ዓይነት፣ በግለሰብ ላይ ተፅእኖ የሚያውለው፣ ከማኅበረሰባዊ መንስዔዎች በመመንጨት ነው፣ በተለይ ከግልሰቡ አፍ መፍቻ ቋንቋው።» - ኤድዋርድ ሳፒር - በአሁኑ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን መነሻ በምንኖርበት ወቅት፣ የአማርኛ ቋንቋ ልሳናዊ አዳብሮት ማተኰር የሚገባው በዘመናዊ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፅንሰ-ሐሳቦች ትርጐማና ተግባራዊ አጠቃቀም ነው። ይሄንም ዓላማ በተጠናቀቀና በተጣራ ደረጃ ለማድረስ፣ የአማርኛ ቋንቋን ቃላት መዝገብን በተገቢ መልኩ፣ የልሳንዊ ብቃት አዳብሮት እና ዝመና መፈፀም ይገባል። ድንቍርና፣ መኃይምነት፣ ኋላቀርነት እና ሐሰተኛ ማኅበራዊ አስተያየቶችና መረጃ-አልባ እኵይ እምነቶችን የሰውን አእምሮ እና ንቃተ-ኅሊናን አደብዝዘው እንደሚያጨልሙት ያህል፣ ዐቢይ እና ዋነኛው መንገድ ልናስወግዳቸውና ልናስቀርፋቸው የምንችለውም፣ በሠናይ ሳይንሳዊና መረጃ-አቀፍ የእውቀት ልማት ከአጣማሪው የሥልጡንና ረቂቅ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም አያይዘን በጥሞና ስናስፋፋ ብቻ ነው። በዚህም ቋሚ ግብ በማመን፣ አቅራቢው ይሄንን ሙዳየ-ቃላት አቀነባብሮ አዘጋጅቷል፣ እና ሙሉ ምኞት ተደርጓል፣ እንደመሠረተ-ድንጋይ ተተክሎ ለትምህርታዊ እና እውቀታዊ ልማት ተገቢ ሚና እንደሚጫወት። ዋና መረጃ ጽሑፍ መጥቀሻ ምንጭ፦ «የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ-ቃላት (እንግሊዝኛ-አማርኛ)»፣ የቃላት ሥያሜና የትርጕም ጥናት ክፍል፣ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዴሚ፣ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፣ ታሕሣሥ 1989 እ.ኢ.አ። 1 የማቴማቲካዊ ምልክቶች ሥርዓተ-ትእምርት፤ የማቴማቲካዊ አኃዝ ቍጥሮች፤ 0 ፦ ዜሮ (አልቦ) 1 ፦ አንድ 2 ፦ ሁለት 3 ፦ ሦስት 4 ፦ አራት 5 ፦ አምስት 6 ፦ ስድስት 7 ፦ ሰባት 8 ፦ ስምንት 9 ፦ ዘጠኝ . ፦ አኃዛዊ ነጥብ ፦ አኃዝ ቤት ስልምታ ምልክት ፦ ቍጥራዊ ቅንባሮት በk አኃዛዊ መሠረት የማቴማቲካዊ ስሌት ምልክቶች፤ + ፦ ሲደመር ከ... − ፦ ሲቀነስበት... ×, ⋅ ፡- ሲባዛ ከ... ÷, / ፡- ሲካፈል ከ... ≈ ፡- ተቃራቢ እኵለት አለው ለ... ≉ ፡- ተቃራቢ እኵለት የለውም ለ... = ፦ ... ያክላል ≟ ፦ የተፈታሽ እኵለት ምልክት ≠ ፦ ... አያክልም ± ፦ ሲደመር ወይም ሲቀነስበት ከ... ∓ ፦ ሲቀነስበት ወይም ሲደመር ከ... ≡ ፦ አቻ ነው ለ... ≢ ፦ አቻ አይደለም ለ... < ፦="" ያንሳል="" ከ...="" ≪="" ፦="" እጅግ="" ያንሳል="" ከ...=""> ፦ ይበልጣል ከ... ≫ ፦ እጅግ ይበልጣል ከ... ≮ ፦ አያንስም ከ... ≯ ፦ አይበልጥም ከ... ≤ ፦ ያንሳል ወይም ያክላል ለ... ≥ ፦ ይበልጣል ወይም ያክላል ለ... ≰ ፦ አያንስም ወይም አያክልም ለ... ≱ ፦ አይበልጥም ወይም አያክልም ለ... ∝ ፡- የምጥጥነት ምልክት ፦ በመቶ (ፐር-ሰንት) ፦ በሺህ (ፐር-ሚል) ⟦𝑥⟧ ፦ የአሐድ ‹ኤክስ› መጥቀሻ ምልክት ፦ የ... ድፍን ጣውልዮሽ ፦ የ... ድፍን እግርግዮሽ ≔ ፦ የፍች ሥያሜ (ብየና) ምልክት ፦ የስብስብ አባልነት ምልክት ∉ ፦ የስብስብ ኢ-አባልነት ምልክት ⊃ ፦ የስብስብ ላዕላዊነት ምልክት ⊂ ፦ የስብስብ ታሕታዊነት ምልክት ⊇ ፦ የስብስብ ፍፁም ላዕላዊነት ምልክት ⊆ ፦ የስብስብ ፍፁም ታሕታዊነት ምልክት ⊄ ፦ የስብስብ ታሕታዊ ኢአባልነት ምልክት ∪ ፦ የስብስብ ውሕደት ምልክት ∩ ፦ የስብስብ ግጥሚያ ምልክት C ፦ የባዕደ-ስብስባዊ አባልነት ምልክት ∅ ፦ ባዶ ስብስብ ∖ ፦ የስብስብ ልይታ ልምክት ፦ የስብስብ ምጥጥናዊ ልይታ ምልክት ∋ ፦ የስብስብ አካታችነት ምልክት ፦ የኵነታዊ ቍጥሮች ስብስብ ℤ ፦ የድፍን ቍጥሮች ስብስብ ፦ የፖዚቲቭ እና ኔጋቲቭ ድፍን ቍጥሮች ስብስቦች ፦ የክፍልፋዊ ቍጥሮች ስብስብ ፦ የኢ-ክፍልፋዊ ቍጥሮች ስብስብ ℂ ፦ የድርብ ቍጥሮች ስብስብ 2 ∃ ፦ ኑረታ ያለው ... አለ ፦ ብቸኛ ኑረታ ያለው ... አለ ∄ ፦ ኑረታ የሌለው ... አለ ∀ ፦ ለሁሉ... ∋ ፦ ከ... ገደብ (ገደቦች) ያቀፈ ∧ ፦ ‹እና› ሎጂካዊ ምልክት ∨ ፦ ‹ወይም› ሎጂካዊ ምልክት ፦ ‹አይ› ሎጂካዊ ምልክት ፦ ‹ፍፁም ወይም› ሎጂካዊ ምልክት ∴ ፡- ስለዚህ ... ∵ ፦ ምክንያቱም ... ⊨ ፦ ... ወደዚህ ግምገማ ያመራል ∼ ፦ የተዛምዶነት ምልክት ፦ ... ወደዚህ ግምገማ ያመራል ⇏ ፦ ወደዚህ ግምገማ አያመራም ⇔ ፦ ... እና ... እርስ ለእርስ ተገምጋሚ ናቸው ⇎ ፦ ... እና ... እርስ ለእርስ ተገምጋሚ አይደሉም □, ■ ፦ የእርግጦሽ ማብቂያ ምልክት ∘ ፦ የቅን ተዛምዶዎች ስክኮሽ ምልክት ∠ ፦ የዘዌ ልኬት መጠን ምልክት ∠ ፦ ዲግሪ ምልክት G rad ፦ የግራድያን እና ራድያን ምልክቶች : ∶∶ ፦ የምጥነት ምልክት ⊥ ፦ ቀጤ-ነክ ለ... ∥ ፦ ትይዩ ለ... ∦ ፦ ትይዩ አይደለም ለ... i ፦ ኢ-ነባራዊ አሐድ ∗ ፦ የኢ-ነባራዊ ጥምድ ምልክት e ፦ እየላዊ ኢ-ተለዋዋጭ π ፦ የክብ ዙሮሽ ኢ-ተለዋዋጭ (ፓይ) ∞ ፦ እልቆ-ቢስ (የእልቆ-ቢስነት ምልክት) የማቴማቲካዊ ቀመራዊ ቅንብሮች ዝርዝር፦ ፦ a እይለ b ፦ a ብዜተ b ፦ ፕሉስ a ፦ ሚኑስ a ፦ a ክፋሌ b ፦ የክፍልፋይ ምልክት ቅንብር ፦ የቅጥልጥል ቅን ተዛምዶ ሥያሜ ቅንፋዊ ቅንባሮት ፦ የእየላዊ ኢተለዋዋጭ ‹ኢ› እይለ a ፦ የa ኵነታዊ ሎጋሪዝም ፦ የa ሎጋሪዝም ከb መሠረት ፦ የa ሎጋሪዝም ከዐሥራዊ መሠረት ፦ የa ካሬ (ክልታዊ) ሥር ፦ የa ሣልሳዊ ሥር ፦ የa ረብዓዊ ሥር ፦ የa ሥር በn ሥርወ-ቍጥር (a ሥርወ n) ፦ የa ንጥረ-እሴት (ፍፁማዊ እሴት) ፦ የa ጠቅላይ ብዜት ፦ a ዝውረ b ፦ a ጥቅሰ n ፦ x ጥቅሰ 1 ወይም x ጥቅሰ 2 ፦ ቀስት (ቬክተር) a ፦ የa ቀስታዊ አሐድ · ፦ ነጥባዊ ብዜት ምልክት × ፦ ሽግራዊ ብዜት ምልክት ፦ የቬክተር a ቀስታዊ ልኬት (ቬክቶሪያዊ ኖርም) ፦ f የx ቅን ተዛምዶ ፦ f የx አምካኝ ቅን ተዛምዶ ፦ የቅን ተዛምዶዎች f የx ከ g የx ቅንብር ትክትዮሽ (ስክኮሽ) ፦f የx፣ y ቅን ተዛምዶ ፦ የአንድ ተለዋዋጭ ቅን ተዛምዶ ማጓደኛ ምልክት ፦ የሁለት ተለዋዋጮች ቅን ተዛምዶ ማጓደኛ ምልክት ፦ የስብስብ መገንቢያ ቅንብር ፦
You might also like